Posts

"የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ" 3ኛ ትምህርት "እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት "

Image
  SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት ) ጥር 3 - 9   3ኛ ትምህርት Jan 11 - 17 እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት ሰንበት ከሰዓት በኋላ ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ሉቃ 15፡11–32፣ ሶፎ. 3፡ 17፣ ኤፌ. 5፡25–28፣ ኢሳ. 43፡4፣ ሮሜ. 8፡1፣ ሮሜ. 5:8፣ ማር. 9:17-29። የመታሰቢያ ጥቅስ፡ አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል” (ሶፎ. 3፡17)። እስቲ የሚከተለውን ሁኔታ ያስቡ፡- የአምስት ዓመት ልጅ በአባቶች ቀን በደንብ ያልተጠቀለለ ስጦታ ይዞ ወደ አባቱ ይመጣል። በደስታ ስጦታውን ለአባቱ ይሰጠዋል። አባትየው “ልጄ፣ ስለ ስጦታህ ግድ የለኝም። እንዲያውም እኔን የሚያስደስት ምንም ነገር ልትሰጠኝ አትችልም። ልትሰጠኝ የምትችለው ሁሉ፣ ራሴ እገዛዋለሁ፣ የምትሰጠኝ ማንኛውም ነገር በገንዘቤ የተገዛ ወይም ከከፈልኩባቸው ቁሳቁሶች የተሰራ ነው። ስለዚህ ስጦታህ ለራስህ ይሁንልህ። አያስልፈልገኝም። ለማንኛውም ግን እወድሃለሁ” እንዳለው ያስቡ። እህ! የዚህ አባት ምላሽ ምን ይመስልዎታል? “ጨካኝ”፣ “ቀዝቃዛ” እና “ስሜት- የለሽ” የሚሉት ቃላት ወደ አእምሯችን ይመጣሉ። እግዚአብሔር እንደዚህ ነው ለእኛ ምላሽ የሚሰጠን? በእርግጥ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን? ለመገመት አስቸጋሪ ቢሆንም - የወደቅን፣ በኃጢአት የተጨማለቅን እና ለክፋት የተጋለጥን ብንሆንም እንኳን - አዎን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን! በሌላ አነጋገር፣ እግዚአብሔር እኛን ወይም የምናመጣቸውን ስጦታዎቻችንን እንደዚያ አባት አይመለከታቸውም። በተቃራኒው፣ በክርስቶስ ብቻ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን። የጎልማሶች ሰን...

"የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ" 2ኛ ትምህርት " ኪዳናዊ ፍቅር"

Image
                                                SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )                                                          ታህሣሥ 26 - ጥር 2                                                                  2ኛ ትምህርት                                                                        Jan 4 - 10                         ...

"የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ" 1ኛ ትምህርት "እግዚአብሔር እንዲሁ ይወዳል::"

Image
SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት ) የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ 1ኛ ሩብ ዓመት 2025 ጥር፣ የካቲት፣ መጋቢት 2017 ዓ.ም. መደበኛ እትም 1ኛ ሩብ ዓመት ከታህሳስ 19 - መጋቢት 19/2017 ዓ.ም 1 ዮሐ. 4:8 እና 16 እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል። መላው መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እውነታ ይመሰክራል። የክርስትና እምነት ማዕከሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ማንነት እምብርት ነው፤ እኛም የምናምነውና የምንሰራው ነገር ሁሉ ማዕከል ፍቅር መሆን አለበት። በዚህ መሠረት ፍቅርን የምንረዳበት መንገድ በእምነታችን እና በድርጊታችን ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ለምሳሌ አንድ ሰው የእግዚአብሔር ፍቅር በሥራ ይገኛል ብሎ ካመነ፣ ኃጢአተኛና ያልበቃ ስለሆነ እግዚአብሔር እንደማይወደው ሊያስብ ይችላል። ከሌሎችም ጋር ባለው ግንኙነት፣ ሰዎችን ይወዳቸው ዘንድ፣ እነርሱ አስቀድመው መልካም ነገር ማድረግ ይኖረባቸዋል ብሎ ያስባል፡- ይህም ለውድቀት መንስኤ ይሆናል። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፍቅር የምንረዳበት መንገድ በእምነታችን እና በልምምዳችን ላይ ትልቅ አንድምታ አለው። ለመሆኑ ፍቅር ምንድን ነው? ፍቅርን እንዲገልጹ አሥር ሰዎችን ቢጠይቋቸው፣ አሥር የተለያዩ ምላሾችን ሊያገኙ ይችላሉ። በክርስቲያኖች መካከል እንኳን፣ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብዙ አፈ-ታሪኮች እና የተሳሳቱ መረዳቶች አሉ። ለምሳሌ ክርስቲያኖች ለሚቀጥሉት ጥያቄዎች የተለያዩ ምላሾችን ይሰጣሉ፡ - የእግዚአብሔር ፍቅር መስጠት ብቻ እንጂ ምላሽ አይጠብቅምን? መለኮታዊው ፍቅር ራሱን መስዋዕት የሚያደርግ ብቻ ነው ወይስ እግዚአብሔር በሰዎች ሐሴት ሊያደርግ ይችላል? የእግዚአብሔር ፍቅር ስሜታዊ ነው? በእርግጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይጠነ...

JESUS " The Way-The Truth-The Life"

Image
 

"እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ"

Image
  "እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤"  1ኛ ቆሮንቶስ 1፡27    ታናሾችን የሚመርጥ ጌታ ነው ያለን! ታናሾችን መምረጡ ደግሞ ከታላቅነቱ ጋር ተጋጭቶበት አያውቅም። ሚዛኑ ከዓለም ሚዛን በእጅጉ ይለያል።   ጌታ ሲመርጥ አያወሳስብም፤ የጌታ መስፈርት ቅንነት፣ ተቀባይነት(ክፍት ልብ)፣ ምልስነት እና ትሁትነት ነው። እነዚህ ባህሪዎች ደግሞ በገንዘብ ብዛት፣ በሥልጣን እርከን፣ የንጉሳዊያን ቤተሰብ በመሆንና በዕውቀት ብዛት የሚመጡ አይደሉም። ወዶ ለተቀበላቸው ሁሉ በምድር ላለው 8 ቢሊየን ህዝብ ሁሉ በነፃ የቀረቡ የባህሪ ምርቶች ናቸው። እንኳን ደስ ያለህ ወንድሜ! እንኳን ደስ አለሽ እህቴ! መላዕክት ያለ ምንም ህፀፅ እና ነቁጥ ሆነው የሚያገለግሉት ይህ ጌታ እነዚህን ባህሪያት በመውረስ ያለ ምንም ከባድ መስፈርት ታገለግሉት ዘንድ መርጧችኋል።  በደካሞቹ ለመገልገል መርጧል። ልብ ላለው(ሲጠብቅም ሲላላም) ይህ ክቡር ዕድል ነው!  እነሆ ይህንን ከመረዳት የተነሳ  “የሚያገለግል ሰው ጠፋ!” የሚለው ድምፅ ከቤተክርስቲያን እንዲጠፋ እንጸልይ። ሁሉም ሰው፣ ይህንን ክቡር ጌታ ለማገልገል የሚሽቀዳደምበትን ዘመን ያምጣልን። መልካም ቀን! ጥር 2፣ 2017 ዓ.ም

"My people are destroyed for lack of knowledge" /"ሕዝቤ እውቀት በማጣቱ ጠፍቷል"/

Image
"My people are destroyed for lack of knowledge: because thou hast rejected knowledge, I will also reject thee, that thou shalt be no priest to me: seeing thou hast forgotten the law of thy God, I will also forget thy children." (Hosea 4:6, KJV) Breakdown and Explanation:   A, "My people are destroyed for lack of knowledge": This is the foundational statement of the verse. It emphasises that the people of Israel are suffering (being "destroyed") because they lack knowledge. B, What kind of knowledge? The "knowledge" here is not just about worldly things or education, but primarily about the knowledge of God, his laws, his character, and his will. It's the understanding of how to live in a covenant relationship with Him. This lack of knowledge leads to spiritual blindness and disobedience, which brings about destruction. C,  "Destroyed": This word doesn't necessarily mean literal annihilation, but rather a state of ruin, moral dec...

"ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች"/ Night is coming, when no one can work."/

Image
  "ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።"  ዮሐንስ 9፡4  አንድ የትምህርት ቤት ወዳጄ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የማነብበው እና ወደ ቤተክርስቲያን የማዘወትረው ዕድሜዬ ሲገፋ ነው ያለኝ አይረሳኝም።  አንዳንድ ጊዜ ትልቅ አካል ባለው ሰው  ውስጥ ትንሽ አዕምሮ እናያለን፤ ይህ መንቃት በነበረበት ዘመን ተኝቶ ያሳለፈ ሰው መገለጫ ነው።    ብዙውን ጊዜ አቅመኛው ዘመናችንን ለራሳችን ሥጋዊ ደስታ ልንሰዋው እንፈልጋለን። የዘመናችንን አመሻሽ ደግሞ "ለነፍሴ ልኑር" በሚል ርዕስ መንፈሳዊያን ሠፈር ጉብኝት እንጀምራለን። ለፈጠረን እና ላዳነን የዘመን ዝቃጭ፣ የዕድሜ ሙጣጭ አይገባውም፣ እርሱ ዋናችን እንጂ አማራጫችን አይደለም። ዕድሜ እና ዓለም ያልበላው ጉልበት በጌታ ማጀት ውስጥ ሊንጠፈጠፍ ይገባል። የእኛ ባልሆነ ነገ ላይ ቀጠሮ አንያያዝ፣ ዛሬያችን ይቀደስ፣ አሁናችንን ለሚገባው መስጠትን እንለማመድ። ወጣትነትን መቀደስ፣ ለበሰለ፣ጥልቀት ላለው ጉልምስና ልብ እና ሰውነትን ያዘጋጃል።  "As long as it is day, we must do the works of him who sent me. Night is coming, when no one can work." John 9:4 I'll never forget a school friend of mine, who told me that I only started reading the Bible and going to church when I got older. Sometimes, we see a small mind in a large body; this is the sign of someone who has spent their waking time sleeping. Often, we want...